When 2 Become 3
"Experience of the phenomenal capacity of our birthing body can give us an enduring sense of our own power as women. Birth is the beginning of life: the beginning of mothering, and of fathering. We all deserve a good beginning."
Welcome!
ማን እንደሆንን
“ጉያ” የአማርኛ ቃል ሲሆን ሕጻን በእናቱ እቅፍ የሚሰማውን ደህንነት የሚያሳይ ዘይቤያዊ አገላለጽ ነው፡፡ የዚህ መድረክ አላማም ይሄው ነው- ነፍሰጡር እናቶች ውድ ልጆቻቸውን በእቅፋቸው ሥር ደህንነታቸው እንዲጠበቅ የሚያስፈልጋቸውን ዕውቀት የሚያገኙበት ቦታ፡፡ የምንሰጠው ትምህርት አላማ የነፍሰጡር ወላጆችን ጭንቀት ማቃለል ነው፡፡ የመጀመሪያው ኮርሳችን ወላጆችን በወሊድ ሂደትና በምጥ ጊዜ፣ ከወሊድ በኋላ፣ በልዩ ሁኔታዎች ምን ማድረግ እንዳለባቸውና በሆስፒታል ምክር ላይ ያተኩራል፡፡ መነሻ ማዕቀፋችን የላማዜን ጤነኛ የወሊድ አሠራር ማዕከል ያደረገ ሲሆን በእናቶችና ሕጻናት ጤና፣ ደህንነትና በተስተካከለ ውልጃ ላይ እናተኩራለን፡፡
ምን እንደምንሠራ
የወሊድ ዝግጁነት ክፍለ ጊዜ
በእርግዝና፣ በምጥና በውልጃ ጊዜ ምን እንደምንጠብቅ የሚገልጽ አጠቃላይ ኮርስ ነው፡፡ በድህረ ወሊድ ምን ማድረግ እንዳለብንና አዲስ የተወለደ ልጃችሁን እንዴት እንደምትንከባከቡ ተጨማሪ አጭር ማብራሪያ ይሰጣል፡፡
የምጥ ሕመም ሕክምና
እርስዎና የህይወት አጋርዎ የተለያዩ የመጽናኛ እርምጃዎችንና ከተለያዩ የምጥ አቀማመጦች በተጨማሪ የሕክምና ባልሆኑ ዘዴዎች አማካኝነት የምጥን ሕመም እንዴት መቋቋም እንደሚቻል ትማራላችሁ፡፡ በተጨማሪም ያሏችሁን የተለያዩ የሕመም ሕክምና አማራጮች እንሸፍናለን፡፡
የጡት ማጥባት ክፍለ ጊዜ
የተገላገሉት በተፈጥሮ ምጥም ሆነ በቀዶ ሕክምና ቢሆን ለእርስዎም ለሕጻኑም ምቾት የሚረዱ የተለያዩ የጡት ማጥባት አቀማመጦች ይማራሉ፡፡ በተጨማሪም ሕጻኑ ጡት ላይ እንዴት በትክክል መለጠፍ እንዳለበት፣ የሕጻኑን አመጋገብ እንዴት እንደምትከታተሉና የጡት ወተት ምርት እንዴት ማነቃቃት እንደሚቻል እና ሌሎች ነገሮች ይማራሉ፡፡
የውልጃ ዝግጁነት
በትምህርት ላይ የተመሰረተ ውሣኔ ላይ ለመድረስና ሥነልቦናዊ ዝግጅት ለማድረግ የሚያስፈልጉዎትን መሳሪያዎች በመስጠት አዲስ ሕጻን ልጅዎን ለመቀበል እንረዳዎታለን፡፡ የወሊድ ሂደትን፣ አዲስ የተወለደ ሕጻን እንክብካቤን፣ የጡት ማጥባት ዝግጅትንና የመሳሰሉትን ማንኛውንም ስጋትዎን እንመለከታለን፡፡
የድህረ ውልጃ ድጋፍ
እናትን ከወሊድ በኋላ መንከባከብ፡፡ አዳዲስ እናቶችና ቤተሰቦቻቸው ከሕጻን ልጆቻቸው ጋር ትስስር ለመፍጠርና በራስ በመተማመን ወደ አዲስ ወላጅነት ሲገቡ የሚያስፈልጋቸውን ጥራት ያለው መረጃ፣ ሥሜታዊና ተግባራዊ ድጋፍ እንሰጣለን፡፡
አዲስ የተወለደ ሕጻን እንክብካቤ
ከሽንት ጨርቅ ቅያሪ እስከ ምገባ አይነቶች፣ የዓይነ ምድር ቀለም ለውጥ፣ ተነጫናጭ ሕጻንን እንዴት ማረጋጋት እንደሚቻል በሁሉም ርዕሶች ላይ ይማራሉ፡፡
የ“ላማዜን” አቀራረብ በመከተል አዳዲስ ወላጆች በእርግዝና፣ በውልጃና በመጀመሪያ የወላጅነት ጊዜያት ትክክለኛ ምርጫ በማድረግ አቅማቸውን ለማሳደግ ጊዜ ጥራት ያለው፣ ያልተዛባ መረጃና ገንቢ ድጋፍ እንሰጣለን፡፡ ከእርግዝና ምክር እስከ አዲስ የተወለደ ህጻንን እንክብካቤ፣ የጡት ማጥባት ድጋፍን፣ የሚሸፍኑ የተለያዩ ርዕሶች “ጉያ” ለእናቶችና ሕጻናት የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ በመስጠት በሕይወትዎ ይህን ጊዜ አስተማማኝ፣ ሰላማዊና ከጭንቀት ነጻ ለማድረግ ሊረዳ ይችላል፡፡