ስለ እኛ

ራዕያችን​

ጥራት ያለው የእናቶችና አዲስ የተወለዱ ሕጻናት መረጃን ተደራሽ ማድረግ መብት ብቻ ሳይሆን ለግለሰቦችም ለማህበረሰቦችም ደህንነት ወሣኝ አስተዋጽኦ ያደርጋል የሚል እምነት አለን፡፡ አላማችን ለነፍሰጡር ወላጆች አስተማማኝ ቦታ መፍጠርና በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሣኔ ማድረግ እንዲችሉና በራሳቸው እንዲተማመኑ ለማድረግ ለማንኛውንም ጥያቄያቸው መልስ የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት ነው፡፡

ተልዕኳችን​

ተልዕኳችን የሴቶችን ልጅ የመውለድ አቅም መገንባት ነው፡፡ ነፍሰጡር እናቶች ጤነኛና አስደሳች የእርግዝና ጊዜ እንዲሳልፉ የሚረዳ ምርጥና ከፍተኛ ጥራት ያለው አገልግሎት የመስጠት ኃላፊነት አለብን፡፡ ለማህበረሰቡ ጥራት ያለው በሰለጠነ ባለሙያ የሚሰጥ ድጋፍና እንክብካቤ ተደራሽ ለማድረግ ሁኔታዎችን እናመቻቻለን፡፡

ፍሬ እሴቶቻችን​

የምንመራባቸው መሠረታዊ እሴቶች በመርህ እና አቋም፣ አቅም ግንባታ፣ ሙያተኝነት፣ ግልጽነት እና የማህበረሰብ ግንባታ ናቸው፡፡

ራዕያችን

ጥራት ያለው የእናቶችና አዲስ የተወለዱ ሕጻናት መረጃን ተደራሽ ማድረግ መብት ብቻ ሳይሆን ለግለሰቦችም ለማህበረሰቦችም ደህንነት ወሣኝ አስተዋጽኦ ያደርጋል የሚል እምነት አለን፡፡ አላማችን ለነፍሰጡር ወላጆች አስተማማኝ ቦታ መፍጠርና በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሣኔ ማድረግ እንዲችሉና በራሳቸው እንዲተማመኑ ለማድረግ ለማንኛውንም ጥያቄያቸው መልስ የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት ነው፡፡

ተልዕኳችን

ተልዕኳችን የሴቶችን ልጅ የመውለድ አቅም መገንባት ነው፡፡ ነፍሰጡር እናቶች ጤነኛና አስደሳች የእርግዝና ጊዜ እንዲሳልፉ የሚረዳ ምርጥና ከፍተኛ ጥራት ያለው አገልግሎት የመስጠት ኃላፊነት አለብን፡፡ ለማህበረሰቡ ጥራት ያለው በሰለጠነ ባለሙያ የሚሰጥ ድጋፍና እንክብካቤ ተደራሽ ለማድረግ ሁኔታዎችን እናመቻቻለን፡ ፡

ፍሬ እሴቶቻችን

የምንመራባቸው መሠረታዊ እሴቶች በመርህ እና አቋም፣ አቅም ግንባታ፣ ሙያተኝነት፣ ግልጽነት እና የማህበረሰብ ግንባታ ናቸው፡፡

ከሁሉ አስቀድሜ ነፍሰጡር በመሆናችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት እወዳለሁ፡፡
እኔ የ“ጉያ” መሥራች አኒ እባላለሁ፡፡ በዚህ ኮርስና በእርግዝናችሁ ጊዜ የግል መሪያችሁ ነኝ፡፡ የ2 ጨቅላ ሕጻናት እናት እንደመሆኔ መጠን በመጀመሪያው እርግዝናዬ የነበረኝን ደስታ፣ ጥርጣሬና ፍርሃት አስታውሳለሁ፡፡ እዚህ የተገኘሁት ስለ እርግዝና እና የምጥን ጠቅላላ ሁኔታ ለማስረዳት፣ አፈታሪኮችን ከእውነታው ለመለየት እና እናንተንም ለዚህ ዝግጁ ለማድረግ ነው፡፡
“ጉያ”ን ከመጀመሬ በፊት በአዲስ አበባ በሚገኙ ሶስተኛ ደረጃ ሆስፒታሎች ለአረጋውያን ህሙማን፣ ለነፍሰጡር ሴቶች፣ ለሕጻናት እና ለድህረ ቀዶ ሕክምና ታካሚዎች በጠቅላላ ሐኪምነት ሠርቻለሁ፡፡ በግልና በሙያ ሕይወቴ እርግዝናን፣ ምጥን፣ የሕመም ሕክምናን በሚመለከት ከነፍሰጡር እናቶች በተደጋጋሚ የተለያዩ ጥያቄዎች ይቀርቡልኝ ነበር፡፡ ይህ ሁላችንም ከእናቶቻችን፣ ከሴት አያቶቻችን፣ ከአክስቶቻችን ወይም ከሴት ጓደኞቻችን ምክር እንደምናገኝና የወደፊት እናቶችን እና አባቶችም ዝግጁ ለመሆን የሚያስፈልጋቸው መደበኛ የመረጃ ምንጭ እንደሌላቸው ለመረዳት አስችሎኛል፡፡
የማስተምራቸው ትምህርቶች በሕክምና ሙያዬ፣ በምርምርና እንደ እናት በግል ተሞክሮዬ ላይ የተመሠረቱ ናቸው፡፡ ያዘጋጀሁት የመጀመሪያ ትምህርት የወሊድ ዝግጁነት የሚል ሲሆን አላማው በአስተማማኝና ጤነኛ ውልጃ፣ በምጥ ሕመም ሕክምናና አዲስ በተወለደ ሕጻን መሠረታዊ እንክብካቤ ዙሪያ ግንዛቤ እንድታገኙ ማድረግ ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ አግባብ ያላቸውን ርዕሶች የሚሸፍኑ ሌሎች ያዘጋጀኋቸው ትምህርቶች አሉኝ፣ ተከታተሉ፡፡
እንደምንገናኝ ብሩህ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

– ተአማኒ
– የተገነባ አቅም
– ሩህሩህ
አዳዲስ ወላጆች በእርግዝና ጊዜ ለራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው ትክክለኛ ውሣኔ ለማድረግ የሚረዳቸውን አቅም ለመገንባት በምርምር ላይ የተመሠረተ፣ ያልተዛባና ገንቢ መረጃ እንሰጣለን፡፡ አካላዊና ስሜታዊ ጥንካሬ በሚጠይቁ የአዲስ ወላጅነት ጥቂት ሳምንታት ሕይወታቸውን አስተማማኝ፣ ሰላማዊና ከጭንቀት ነጻ ለማድረግ ጤነኛ ሚዛን ለመጠበቅ ከአዳዲስ ወላጆች ጋር እንሠራለን፡፡
ይህ ድጋፍ በመጀመሪያው የሕይወት አመት እስከ ህፃናት የመጀመሪያ ወራቶች እንክብካቤ እና በልዩ ተስማሚ ድጋፍ እንዲሁም በተለየ የግል ፕሮግራም ታግዞ ሊቀጥል ይችላል፡፡
ወላጅነት አጋርነት መሆኑንና ሁሉም ትምህርቶች የወደፊት አባቶችንም ለማካተት የተቀረጹ መሆናቸው እናምናለን፡፡ በእርግዝና ጊዜ፣ በምጥና በሕጻን እድገት ጊዜ ሁሉ አቅማችሁ እንዲያድግና ተሳታፊ እንድትሆኑ እንፈልጋለን፣ በኮርሶቻችን በዚህ የአካላዊ፣ ስሜታዊና መንፈሳዊ የውልጃ ሂደትና ከዚያም ባሻገር ከአጋሮቻችሁ ጋር ተሳታፊ ለመሆን የሚያስፈልጋችሁን ክህሎት ታገኛላችሁ፡፡ለጥንዶች የተዘጋጀ የገጽ ለገጽ ኮርስና ተግባራዊ መልመጃ አለ፡፡ እንዳንዱ ክፍለ ጊዜ 2 ርዕሶችን በጠቅላላው 4 ክፍለ ጊዜ የሚሸፍን ሆኖ 90 ደቂቃ ይፈጃል፡፡ 

ከመስራቿ

ከሁሉ አስቀድሜ ነፍሰጡር በመሆናችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት እወዳለሁ፡፡

እኔ የ“ጉያ” መሥራች አኒ እባላለሁ፡፡ በዚህ ኮርስና በእርግዝናችሁ ጊዜ የግል መሪያችሁ ነኝ፡፡ የ2 ጨቅላ ሕጻናት እናት እንደመሆኔ መጠን በመጀመሪያው እርግዝናዬ የነበረኝን ደስታ፣ ጥርጣሬና ፍርሃት አስታውሳለሁ፡፡ እዚህ የተገኘሁት ስለ እርግዝና እና የምጥን ጠቅላላ ሁኔታ ለማስረዳት፣ አፈታሪኮችን ከእውነታው ለመለየት እና እናንተንም ለዚህ ዝግጁ ለማድረግ ነው፡፡ 

“ጉያ”ን ከመጀመሬ በፊት በአዲስ አበባ በሚገኙ ሶስተኛ ደረጃ ሆስፒታሎች ለአረጋውያን ህሙማን፣ ለነፍሰጡር ሴቶች፣ ለሕጻናት እና ለድህረ ቀዶ ሕክምና ታካሚዎች በጠቅላላ ሐኪምነት ሠርቻለሁ፡፡ በግልና በሙያ ሕይወቴ እርግዝናን፣ ምጥን፣ የሕመም ሕክምናን በሚመለከት ከነፍሰጡር እናቶች በተደጋጋሚ የተለያዩ ጥያቄዎች ይቀርቡልኝ ነበር፡፡ ይህ ሁላችንም ከእናቶቻችን፣ ከሴት አያቶቻችን፣ ከአክስቶቻችን ወይም ከሴት ጓደኞቻችን ምክር እንደምናገኝና የወደፊት እናቶችን እና አባቶችም ዝግጁ ለመሆን የሚያስፈልጋቸው መደበኛ የመረጃ ምንጭ እንደሌላቸው ለመረዳት አስችሎኛል፡፡ 

የማስተምራቸው ትምህርቶች በሕክምና ሙያዬ፣ በምርምርና እንደ እናት በግል ተሞክሮዬ ላይ የተመሠረቱ ናቸው፡፡ ያዘጋጀሁት የመጀመሪያ ትምህርት የወሊድ ዝግጁነት የሚል ሲሆን አላማው በአስተማማኝና ጤነኛ ውልጃ፣ በምጥ ሕመም ሕክምናና አዲስ በተወለደ ሕጻን መሠረታዊ እንክብካቤ ዙሪያ ግንዛቤ እንድታገኙ ማድረግ ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ አግባብ ያላቸውን ርዕሶች የሚሸፍኑ ሌሎች ያዘጋጀኋቸው ትምህርቶች አሉኝ፣ ተከታተሉ፡፡ 

እንደምንገናኝ ብሩህ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ከመስራቿ
ታማኝ
የተገነባ አቅም
ሩህሩህ

አዳዲስ ወላጆች በእርግዝና ጊዜ ለራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው ትክክለኛ ውሣኔ ለማድረግ የሚረዳቸውን አቅም ለመገንባት በምርምር ላይ የተመሠረተ፣ ያልተዛባና ገንቢ መረጃ እንሰጣለን፡፡ አካላዊና ስሜታዊ ጥንካሬ በሚጠይቁ የአዲስ ወላጅነት ጥቂት ሳምንታት ሕይወታቸውን አስተማማኝ፣ ሰላማዊና ከጭንቀት ነጻ ለማድረግ ጤነኛ ሚዛን ለመጠበቅ ከአዳዲስ ወላጆች ጋር እንሠራለን፡፡ 

ይህ ድጋፍ በመጀመሪያው የሕይወት አመት እስከ ቅድመ ልጅነት እንክብካቤ እና በልዩ ተስማሚ ድጋፍ እንዲሁም በተለየ የግል ፕሮግራም ታግዞ ሊቀጥል ይችላል፡፡

ወላጅነት አጋርነት መሆኑንና ሁሉም ትምህርቶች የወደፊት አባቶችንም ለማካተት የተቀረጹ መሆናቸው እናምናለን፡፡ በእርግዝና ጊዜ፣ በምጥና በሕጻን እድገት ጊዜ ሁሉ አቅማችሁ እንዲያድግና ተሳታፊ እንድትሆኑ እንፈልጋለን፣ በኮርሶቻችን በዚህ የአካላዊ፣ ስሜታዊና መንፈሳዊ የውልጃ ሂደትና ከዚያም ባሻገር ከአጋሮቻችሁ ጋር ተሳታፊ ለመሆን የሚያስፈልጋችሁን ክህሎት ታገኛላችሁ፡፡ 

amAM